“አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ‘ከባድ ወንጀሎች’ ብሎ በሚገልፃቸዉ አደገኛ ወንጀሎች ተጥለቅላቃለች፤በከተማይቱ ታይቶ በማያዉቅ ሁኔታ ከባድ ወንጀሎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች የፖሊስ መምሪያዎችና ንዑስ የፖሊስ ጣቢያዎች በብዛት እየተመዘገቡ ነዉ….ቅሚያ ቤት ሰብሮ ስርቆት ዉንብድና ወዘተ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቷል….ባለፉት ሃያ አመታት በከተማይቱ አጋጥሞ በማያዉቅ ሁኔታ የዜጎች ሰላም ደህንነትና በሰላም ወቶ መግባት አደጋ ላይ ወድቋል….መንግስት ቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ እንዴትና በምን መንገድ ሊጠበቅ እንደቻለ በመገምገም ጠቃሚዉንና የተሻለዉን ከመኮረጅና ከፍ ሲልም የቀድሞዉን መልካም ልምዶች ከማስፋፋትና ከማጠናከር ይልቅ ጥቂቶችን በመወንጀልና እገሌ የእገሌ ኔት ወርክና ደጋፊ ነዉ በሚል ፍረጃ የአዲስ አበባን ፖሊስ ኮሚሽንን ጠንካራ ክፍሎች በማዳከም የሰራዊቱን ሞራልና ተነሳሽነት በማኮላሸት ነባር በሳልና ጠንካራ አመራሮችን ከምደባ ዉጪ በማድረግ አንዳንዶቹን ደግሞ ረዥም ጊዜ ከሰሩበትና ከፍተኛ ልምድ ካገኙበት የስራ ክፍል በማዘዋወር ከተማዋ የወንጀለኞች መፈንጫ እንድትሆን አደርጓል…..
“ዛሬ በአዲስ አበባ ላይ የሚከተሉት ወንጀሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየታዩ በመሆኑ ዜጎች የራሳቸዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እመክራለሁ
“1- ቅሚያ
“A- የሞባይል የሴቶች ቦርሳና ሌሎች ዉድ ንብረቶች ቅሚያ
“B- ከባንክና ከሌሎች የንግድ ተቋማት ገንዘብ ይዘዉ በሚወጡ ዜጎች ላይ የሚፈፀም ቅሚያ
“C-በሞተር ሳይክል የሚፈፀም ቅሚያ
“2-ዉንብድና
“A-ከፍተኛ ገንዘብ ይንቀሳቀስባቸዋል ተብሎ በሚገመቱ የንግድ፣የመንግስትና የሃይማኖት ተቋማት ላይ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያ
“B-በምሽት መንገድ በመዝጋት መኪኖችን በማስቆም በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያ
“C-በቀንና በለሊት በመኖሪያ ቤት ወይም በድርጅቶች ዉስጥ በመግባት በጦር መሳሪያ አስገድዶ ዝርፊያ
“3-የመኪና ስርቆት
“A-መኪናን በተመሳሳይ ቁልፍ ወይም ሌሎች ቴክኒኮችን በመጠቀም በመክፈት ሞተር አስነስቶ መስረቅ(መሰወር)
“B-የመኪና አካላትን በዉድቅት ለሊት በመኖሪያ ቤት ወይም በድርጅት ቅጥር ጊቢ በመግባት አዉልቆ መዉሰድ
“C-በቀን የሚፈፀም የመኪና አካላት ስርቆት
“4- ማስገደድ
“A-በናይት ክለቦችና ተመሳሳይ የመዝናኛ ቦታዎች ከተስተናጋጆች ጋር በመመሳሰል በመፀዳጃ ቤቶችና በመዝናኛዎቹ አቅራቢያ በግዳጅ የሚፈፀም ዘረፋ
“B-ጨለማን ተገን በማድረግ አንዳንዴም በጠራራ ፀሀይ በተለያዩ አካባቢዎች በጉልበት በስለትና በጦር መሳሪያ በማስገደድ ዘረፋ(ሀንግ)
“ራሳችሁን ጠብቁ።”