በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደረሰው ጥቃት ለኤምባሲው በቂ ጥበቃ ባለመኖሩ የተከሰተ መሆኑንና በድርጊቱም ማዘኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ተወካይ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ተቃውሞ አቅርበዋል ። ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲውን ተቆጣጥረው ሰንደቅ ዓላማ ማውረዳቸው በቂ ጥበቃ አለመኖሩን፣ ድርጊቱን በፈፀሙ አካላት ላይ ጀርመን አስፈላጊውን እርምጃ አለመውሰዷን ፣ የኤምባሲው መደበኛ ስራ ማስተጓጎል ጉዳይ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ተወካይ ሄይኮ ኒዣኬ አቅርባለች ። ሀላፊውም በበኩላቸው በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደረሰው ጥቃት ተቀባይነት እንደሌለው ጠቁመዋል፡፡
የጀርመን መንግስት ድርጊቱን በቅርብ በመከታተል አጣርቶ አስፈላጊን ማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።