ወንድማችን ጉዱ ካሳ (አለማየሁ በላይነህ) አረፈ !

ጀግናው እና ሀገር ወዳዱ ወንድማችን አቶ አለማየሁ በላይነህ
( ጉዱ ካሳ ) በክብር ወደ ፈጣሪ ሸኝተነዋል:: አምላክ ነፍሱን በመንግስተ ሰማያት ያኑርልን :: ስራዎቹ ለዘላለም ይታወሳሉ ለቤተሰቦቹ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልኝ 🙌 እንዲህ አይነት ሀገር ወዳድ ጀግና ሰው በአካል ቀርቤ ሳላገኘው ቢለየንም በክብር ግን ሸኝቸዋለሁ :: በሰላም እረፍ

ለወንድሜ ለአለማየሁ በላይነህ ስንብት
************************
ሰንቀህ አልነበር ፣ በጣም ትልቅ ተስፋ
ምነው ሐሳብ ቀየርክ፣ ጥንካሬህ ጠፋ
በአስገምጋሚ ድምፅህ፣ በፓል ቶክ ስትመጣ
አንዴ በሽው ሽው፣አንዴ በአደራ ድምፅ ፣የወገን ባላንጣ
መዋያ ማደሪያ ፣መግቢያ ስናሳጣ
ያ ጨለማ ጊዜ፣ትዝታው እየመጣ
ረበሸኝ በጣም ፣ዛሬ አንተን ስናጣ !
ተመኘሁ ትላንትን፣ ዛሬን ተፀየፍኩት
አገር ሻጭ ሲበዛ፣ ራሴን ጠየኩት
ያ ትንታጉ ጓዴ፣የማይተኛው ሌሊት
ምነው ጥሎን ሄደ፣ሳንማከር ድንገት ?
ምነው ዛሬ ብትኖር፣መቅረጫህን ጠምደህ
አትተኛ ኮሮጆ፣ብለህኝ አንቅተህ
ስንት ተዐምር በሠራን፣ዛሬም እንደ ትላንት
የከሀዲን ሠፈር ፣ብንለቅበት እሳት ?
ምንድነው ያስከፋህ፣እንዲህ ያስጨከነህ?
ዘመኑ ሲከፋስ፣ማን ጥለህ ሂድ አለህ ?
አፈሩ ይቅለልህ ፣ሌላ ምን እላለሁ
ጉዱ ካሣ ሄዷል፣እርሜን አውጥቻለሁ ።
ሐያሉ እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት ። ለደግዋ ባለቤትህና ለምትወዳቸው ልጆችህ ፣ እንዲሁም ለመላው ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎችህ ሁሉ መፅናናትን ይስጣቸው ! አፈሩ ይቅለልህ ወንድም አለም !

Dereje Mengesha. Berlin. 18.07.2020

Recommended For You

About the Author: admin