አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የሚታየው በጸጥታው ምክር ቤት ሳይሆን በአፍሪካ ህብረት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚስትር ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የተፋሰሱ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይቱም ታላቁ የህዳሴ ግድብ የታችኞቹን የተፋሰሱ ሀገራት በማይጎዳ መልኩ በፍትሀዊነት እና በምክንያታዊነት የሚጠቅም የጋራ ፕሮጀክት መሆኑን አቶ ደመቀ አብራርተዋል፡፡ሱዳን እና ግብጽ በማይገባ መልኩ የህዳሴውን ግድብ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት እና የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት በመውሰድ አለም አቀፋዊ እና የደህንነት ጉዳይ አደርገውታልም ነው ያሉት፡፡ሁለቱ ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን ሚና ዝቅ በማድረግ የጀመሩትን እንቅስቃሴ በመተው ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲያመጡት እና የቅኝ ግዛት ዘመን አካሄድን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የውይይት መድረኩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ ለሀገራቱ ማብራሪያ ለመስጠት ያለመ ነው፡፡ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcastingዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevisionትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!