Sibhat Nega, Master of the TPLF is arrested.

ሕወሓት በ1967 ዓ.ም. ሲመሠረት አንደኛው መሥራችና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ)፣ ከባለቤታቸው ሌተና ኮሎኔል ፀአዱ ሪች ጋር ተከዜ አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Dejene Assefa

 በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ የተወሰደባቸው የጁንታው አመራሮች————/———/—————= ሴኮቱሬ ጌታቸው – (መብረቃዊ)= ዘርአይ አስግዶም – የኢቢሲ ሃላፊ : የብሮድካስት ባለስልጣን ዳይሬክተርና ቀንደኛ የጁንታው አመራር= አበበ ገብረመድህን – የድምጸ ወያኔ ሃላፊ= ዳንኤል አሰፋ – የጌታቸው አሰፋ ወንድም እና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበረ ሲሆን አራቱም ከነአጃቢዎቻቸው ተደምስሰዋል (ተገድለዋል)!!!!….በቁጥጥር ስር የዋሉ 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ——–/———–/—————-= ቅዱሳን ነጋ – የስብሃት ነጋ እህትና ቀንደኛ አመራር= ቴድሮስ ሃጎስ – የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበረ (ቀንደኛ አመራር እና የጌታቸው ረዳ የቅርብ ወዳጅ የነበረ)= ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ= ገብረመድህን ተወልደ – የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ = ተክለወይኒ አሰፋ – ነባር የትህነግ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል እና የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ= ወልደጊዮርጊስ ደስታ – መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ:= አባዲ ዘሙ – የመለስ ታማኝ (ቀንደኛ አመራር : በሱዳን አምባሳደር የነበረ እና እንደምታዩት ጋዜጠኛውን አንበርክኮ ቃለመጠይቅ የሚያደርግ..)= ወ/ሮ ምህረት ተክላይ – የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም= ብርሃነ አደም – የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበረ …. ሁሉም በቁጥጥር ስር ውለዋል:: በቃ!!!……የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመን ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ሲሉ እንዳልነበር መጨረሻቸው እንዲህ ሆነ!!!! ፈራጅ በሰማይ አለ!!!ኢትዮጵያ በክብር ትቀጥላለች!!!!ሁሉም ለራሴ ብሎ ይስማ!!!!

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የኃይል ሥምሪት መምርያ ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ዓርብ ታኅሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፣ በተጨማሪም ከመከላከያ ሠራዊት የከዱት ኮሎኔል ክንፈ ታደሰና ኮሎኔል የማነ ካህሳይ፣ እንዲሁም አስገደ ገብረ ክርስቶስ የተባለ ከመሀል አገር በመሄድ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ኃላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የሜጀር ጄኔራል ኃየሎም አርዓያ ባለቤት የነበሩና ኑሮዋቸውን በአሜሪካ አድርገው የቆዩት፣ በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ሕወሓትን ተቀላቅለው የነበሩት ወ/ሮ አልጋነሽ መለስ፣ በኦፕሬሽኑ ወቅት ለማምለጥ ሲሞክሩ ገደል በመግባት ሕይወታቸው ማለፉን ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አስታውቀዋል፡፡

የሕወሓት ቁንጮ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ከተደበቁበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀዋቸው እንደነበር አስረድተው፣ ‹‹ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ሥር አውለውታል፤›› ብለዋል።

አቶ ስብሃት ላለፉት 27 ዓመታት የማተራመስ ስትራቴጂ በመንደፍ ያስተባበሩና ያደራጁ፣ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሠራዊቱን ያስጨፈጨፉ የሕወሓት ቁንጮ አመራር መሆናቸውን፣ ባለቤታቸው ሌተና ኮሎኔል ፀአዱ ደግሞ ቀደም ሲል በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሐኪም የነበሩና በኋላም በጡረታ የተገለሉ መሆናቸውን ብርጋዴር ጄኔራሉ አስረድተዋል፡፡

ከመከላከያ ሠራዊቱ የከዱ የቡድኑ አመራሮች ታጣቂውን ኃይል በማሠልጠንና በማዋጋት እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሠሩ መቆየታቸውን ጄኔራል መኮንኑ አስታውሰው፣ በመጨረሻም ለሕወሓት አመራሮች ዙሪያ ጥበቃ ሲያስተባብሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ሐሙስ ታኅሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት የአገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ፣ ዘጠኝ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች እጃቸውን መስጠታቸውንና አራት የቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ እንዳሉት የቡድኑ ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም፣ የድምፀ ወያኔ ኃላፊ አቶ አበበ አስገዶም፣ እንዲሁም የትግራይ ክልል የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ (የአቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም) ከሾፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት፣ በትግራይ ሕዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ ተደምስሰዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉት የቡድኑ ቁልፍ አባላት የቀድሞ የትግራይ ክልል አፈ ጉባዔና የአቶ ስብሃት እህት ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ (ባለቤታቸው የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋይ በርኼ)፣ የክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊና የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ የማረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተክለወይኒ አሰፋ፣ የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረ መድኅን ተወልደ፣ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበሩት አቶ አባዲ ዘሙ፣ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ ደስታ፣ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ የክልሉ ምክር ቤት ሕግ አማካሪ  ወይዘሮ ምሕረት ተክላይ፣ እንዲሁም የክልሉ የንብረትና ግዥ የሥራ ሒደት ኃላፊ አቶ ብርሃነ አደም መሐመድ ናቸው፡፡

 የሕወሓት ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር የዋሉት በጫካና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ጠንካራ አሰሳ መሆኑንም ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋዬ ገልጸው፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የጥፋት ቡድኑ አባላት እንዲደመሰሱና በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ያላሰለሰ ድጋፍ ላደረገው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሥጋናውን ማቅረቡን ጠቁመው፣ አሁንም ድጋፉን እንዲቀጥል አሳስበዋል። ሠራዊቱ ወንጀለኞቹን አድኖ ለመያዝ ቃል በገባው መሠረት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑንም አክለዋል።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ሌሊት በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ በሕወሓት አመራሮች ትዕዛዝ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሰጡት ትዕዛዝ ሕግ የማስከበር ዘመቻ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ሠራዊቱም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በርካታ የክልሉን ከተሞችና ዋና ከተማዋን መቀሌ በቁጥጥር ሥር ካዋለ ጀምሮ በርካታ የሕወሓት አመራሮችና ወታደራዊ ኃላፊዎች መደምሰሳቸውና በቁጥጥር ሥር መዋላቸው መገለጹ አይዘነጋም፡፡

እስካሁን ድረስ የሕወሓት ሊቀመንበርና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ)፣ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋና ሌሎች የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ እንዲሁም ከነባር አመራሮች አቶ ሥዩም መስፍንና አቶ ዓባይ ፀሐዬን የመሳሰሉት የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ነገር ግን የአገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት እነሱን ለመያዝ አደን መቀጠላቸው ተነግሯል፡፡

The public Ethiopian News Agency quoted Brig. Gen. Tesfaye Ayalew as saying that Sebhat Nega, a founding member of the TPLF, had surrendered during the operation.

Sebhat is considered a magnate within the TPLF and is known for having built a multibillion-dollar business empire in Ethiopia over the 27 years the group was in power.

On Thursday, the army said nine other key TPLF officials had been captured, while four others were neutralized in the ongoing law enforcement operation.

An unspecified number of soldiers were killed last year and a sizable amount of military hardware had been looted by TPLF forces, prompting the government to launch a massive law enforcement operation.

On Nov. 28, Prime Minister Abiy Ahmed declared the operation complete, saying what remained was apprehending the TPLF leadership and their militants, reconstruction and rehabilitation in the restive region, and putting in place the structures of an interim administration for Tigray.​​​​​​​

Recommended For You

About the Author: admin