bolsa de pierna decathlon
Adidas Stan Smith
sadarināšanās gredzeni
χρυσσες πλατφορμες
napihljivi fotelj merkur
nike air zoom pegasus 36 w
replika spor ayakkabı toptan
ted baker aurinkolasit
moschino tričko
νακ παπουτσια πεδιλα
Adidas Stan Smith
sadarināšanās gredzeni
χρυσσες πλατφορμες
napihljivi fotelj merkur
nike air zoom pegasus 36 w
replika spor ayakkabı toptan
ted baker aurinkolasit
moschino tričko
νακ παπουτσια πεδιλα
ሥለ ኑረንበርግ ኢንተግራሲዮን ምክርቤት ምንነትና የምርጫ ሂደት ግንዛቤ ማስጨበጫ አጭር ጽሁፍ
የኑረንበርግ ኢንተግራሲኦን ምክርቤት በከተማው ነዋሪ የሆኑ የሊላ አገር ዜግነት የነበራቸው ወይንም ያላቸው ሰዎች በቀጥታ ድምጽ በሚመርጧቸው ተወካዮች የሚዋቀርና ለነዚህ ኗሪዎች ጉዳዮች ድምጽ በመሆን ከከተማው አስተዳደር ጋር በትብብር የሚሠራ ምክርቤት ነው። ዋናው የምክርቤቱ ተልዕኮ የሚወክላቸውን የማህበረሠብ ክፍሎች የኑሮ ሁኒታ እንዲሻሻል በማድረግ ከቀሪው የከተማ ነዋሪ ጋር በዕኩልነትና በሠላም አብረው የሚኖሩበትን ሁኒታ ማመቻቸት ነው። ምክር ቢቱ በየስድስት ዓመቱ እንደ አዲስ የሚመረጥ ሲሆን ዋና ዋና ተግባራቱ የሚከተሉት ናቸው
ለከተማው ምክር ቤትና ለከተማው አስተዳደር በውጭ ዜጎችና ቀድሞ የውጭ ዜግነት በነበራቸው የከተማው ነዋሪዎች ጉዳዮች ዙሪያ በአስተዳደሩ ጥያቂ ወይንም በራስ ተነሳሽነት በሚነሱ አጀንዳዎች ላይ አማካሪ በመሆን ይሠራል።
ምክር ቤቱ የሚያቀርባቸው ጥቆማዎችና ግብዓአቶች ባጭር ጊዚ ውስጥ በከተማው ምክርቤት የኢንተግሪሽን ኮሚሽን የመደመጥና ተገቢውን መልሥ የማግኘት መብት አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም የከተማው አስተዳደር የውጭ ዚጎችን ጉዳይ በተመለከተ ለመከወን የሚያስባቸውን ነገሮች በቅድሚያ ለኢንተግራሲዮን ምክርቤት ማሳወቅ ግዲታው ነው።
የኑረንበርግ ኢንተግራሲዮን ምክርቢት በየጊዝው የራሱ እንቅስቃሲዎችና መድረኮች ይኖሩታል። ለምሳሌ ብንወስድ ዓመታዊው የባህል ተሻጋሪ ሥራዎች አሸናፊ ሽልማትን የመሰሉ መድረኮች። የምክርቤቱ ቢሮ እነዚህን እንቅስቃሲዎች ያቀነባብራል፣ ምክር የሚፈልጉ ነዋሪዎችን ጥያቂዎች ያስተናግዳል።
የኑረንበርግ ኢንተግራሲዮን ምክርቤት ምርጫ ሂደት ምን ይመስላል?
ለምክርቤቱ በተወካይነት የሚላኩት ግለሰቦች ከተገለጸው የማህበረሰብ ክፍል በቀጥታ የሚመረጡ ሲሆን የቦታ ክፍፍሉን የተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም በከተማው ውስጥ የሚታየውን የማህበረሰብ ስብጥር እንዲመስል ተደርጎ የሚዋቀር ሲሆን በተለይ በጣም አናሳ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳይጎዱ ጥንቃቂ ይደረጋል።
የምክርቤቱ አወቃቀር
ምክርቤቱ 30 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ነዋሪዎቹ የመጡባቸውን የዓለም ክፍሎች ታሳቢ በማድረግ በ 4 ግሩፖች ይከፈላሉ። እነዚህ ግሩፖች የሚያገኙት መቀመጫ ብዛት ደግሞ በኑረንበርግ የህዝብ ብዛት ውስጥ ያላቸውን ደረጃ እንዲያንጸባርቅ ይደረጋል። በዚህ አሰራርም
የአውሮፓ ዩንየን ግሩፕ 8 መቀመጫ
ከአውሮፓ ዩንየን ውጭ ያለ አውሮፓ 9 መቀመጫ
አፍሪካ፣ አስያ፣ አሚሪካና ኦሲያኒያ 8 መቀመጫ
የተመላሽ ጀርመኖች ወይንም አውስሲድለር 5 መቀመጫ
ይኖራቸዋል።
በግሩፖቹ ውስጥም በድምጽ ብልጫ ብቻ ሳይሆን አካታች የሆነ ስብጥር እንዲኖር በሚያደርግ አሠራር መቀመጫዎቹ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል። ለምሳሌ የአውሮፓ ዩንየን ግሩፕ ውስጥ ቢያንስ ከተለያዩ አምስት አገራት የመጡ ተወካዮች ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ ግድ ነው!
መምረጥ የሚችለው ማን ነው?
እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ቀድሞ የውጭ አገር ዜግነት የነበረው ወይንም አሁንም ያለውና በኑረንበርግ ከተማ ላለፉት 6 ወራት ያለማቋረጥ ተመዝግቦ የኖረ ሠው የመምረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለመራጮች በደብዳቤ የምርጫ ካርድ እንዲደርሳቸው ይደረጋል።
መመረጥስ የሚችለው ማን ነው?
ለምርጫ ለመወዳደር ዕጩዎች ቢያንስ ለሦስት ዓመታት ያለማቋረጥ በኑረንበርግ ከተማ ተመዝግበው የኖሩ መሆን አለባቸው። ተወዳዳሪዎቹ በግል ወይንም ከኣላማ አጋሮቻቸው ጋር በግሩፕ ሆነው ለምርጫ መቅረብ ይችላሉ።
የምርጫው ደንብ ምን ይመስላል?
እያንዳንዱ መራጭ 12 ድምጾች አሉት። ለአንድ ዕጩ ከአንድ እስከ ሶስት ድምጽ መስጠት ይችላል። በዚህ መልክ ለሚፈልጋቸው ዕጩዎች በሚፈልገው መጠን 1 ወይ 2 ወይ 3 ድምጽ በመስጠት ድምጾቹን ማከፋፈል ይችላል። ዋናው ነግር መራጩ የሠጣቸው ድምጾች በድምሩ ከ 12 በላይ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ይህ ከሆነ ሁሉም ድምጹ ይሠረዝበታል።
የምርጫው ቀን ዕለተ ዕሁድ 09.10.2022 ከጠዋቱ 8 ሠዓት እስከ ምሽቱ 18 ሠዓት ሲሆን ቦታው እንደ መኖሪያ ሠፈራችሁ በምርጫ ካርድ ደብዳቤው ላይ ይገለጻል።
ሁላችንም በምርጫው ቀን በሠዓቱ በምርጫ ጣቢያ ተገኝተን ለኛ ጉዳይ ሊሠሩልን ይችላሉ የምንላቸውን ሠዎች በሦሥት ድምጽ በመምረጥ ለራሳችንም ሆነ ለኮሚኒቲኣችን ጠቃሚ ሥራ እንስራ!!!
ድ ም ጽ ዎ ን ይ ጠ ቀ ሙ!!!