የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ከሰላሳ ኤምባሲዎች በላይ ከነሀሴ 15, 2013 በኋላ እንደሚዘጋ ይፋ አድርጓል። በሚዘጉ ኤምባሲዎች ውስጥ የሚሰሩ ከ300 በላይ ዲፕሎማቶች ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ለኤምባሲዎቹ በደብዳቤ አሳውቋል።ከሚዘጉ ኤምባሲዎች በተጨማሪ በማይዘጉ ኤምባሲዎችም የሚሰሩ ሁሉም ዲፕሎማቶች ከዋና አምባሳደርና ፋይናንስ ሰራተኛው ውጭ እንዲመለሱ ትዕዛዝ መተላለፉን አሳውቋል፡፡እንዲዘጉ ከተወሰነባቸው ኤምባሲዎች ውስጥ 1. ከአውሮፓ- ቱርክ (አንካራና ኢስታቡል)፣ ጀርመን (ፍራንከፈርት)፣ አየርላንድ (ደብሊን)፣ ስዊድን (ስቶክሆልም) የተዘጉ ሲሆን በሌሎች ኤምባሲዎች የሚገኙም ዲፕሎማቶች በሙሉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡2. ከአፍሪካ – 10 ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች – አልጀሪያ፣ ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ጋና፣ ናይጀሪያ፣ ኮትዲቯር፣ ዚምባብዌ፣ ታንዛኒያ፣ ርዋንዳና ሱዳን (ገዳሪፍ)3. ከሰሜን አሜሪካ – ሎስ አንጀለስና ሚኒሶታ – የተዘጉ ሲሆን በዋሽንግተንና በካናዳ (ኦታዋ) ኤምባሲዎች ያሉ ዲፕሎማቶች ሁሉም በሚባል ደረጃ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡4. ከደቡብ አሜሪካና ካሪቢያን – ብራዚልና ኩባ5. ከኤዥያ – አውስትራሊያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሕንድ (ሙምባይ)6. ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ኦማን፣ ባህሬን፣ ሊባኖስ ይገኙበታል፡፡በሚዘጉ ኤምባሲዎች ዋናው አምባሳደርና የፋይናስ ሰራተኛው፣ በቆንስላዎች ደግሞ የፋይናንስና አስተዳደር ባለሞያው ንብረቶች ለመሸከፍና ለመሸጥ ሲባል ለጊዜው ይቆያሉ ተብሏል።