የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ የአዲስ አበባ ፍቅርዋን ለመግለፅ አንዱን ጎዳናዋን አዲስ አበባ ብላ ሰይማለች። ከ ጎርጎረሳዉያኑ 2004 ጀምሮ በእህትማማችነት ዝምድናን የመሰረቱት የጀርመንዋ ላይፕዚሽ ከተማ እና አዲስ አበባ ወዳጅነታቸዉ ጥልቅ ነዉ ። በላፕዚሽ ከተማ ዩንቨርስቲ የአማርኛ እና ግዕዝ ቋንቋ ትምህርት እና ጥናት ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል። በነገራችን ላይ ላይፕዚሽ ከተማ አንዱን የከተማዋን አደባባይ አዲስ አበባ ብላ የሰመችዉ ዛሬ ሳይሆን የዛሬ 5 ዓመት በጎርጎረሳዉያኑ 2015 መስከረም 29 ነዉ። ከዝያ ስያሜዉን ረዘም በማድረግ በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ ከአነስተኛ አደባባይ ተነስቶ ወደ ጎዳና የሚወስድን 50 ሜትር መንገድን አዲስ አበባ ፕላትዝ ብላ ሰይማለች። እንዲህ ነዉ እህትማማችነት !